ይህ ደንብ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከጸደቀበት ከጥቅምት ፳፻፲፮ ዓ.ም ጀምሮ በውጭ ሀገረ በሚገኙ አህጉረ ስብከት እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ሁሉ የጸና ይሆናል፡፡
Qale Awadi - ቃለ አዋዲ
Ethiopian Orthodox
Tewahedo Church Bylaw
Oct. 2023 (Tikimit 2016 E.C.)
(No. 6/2016) for Dioceses/ Archdioceses Parishes
Ecclesiastical Administration Council Outside of Ethiopia.
This regulation, approved by the Holy Synod
in October 2023, will remain in effect for all
dioceses and local churches outside of
Ethiopia.
ማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ካህን፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና
ባልሰጠውና በሀገረ ስብከቱ አስተዳደራዊ መዋቅር
ሥር በማይመራ ማንኛውም ቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት መስጠት ፈጽሞ አይችልም።
ቃለ ዐዋዲ - አንቀጽ ፲፮/17
ልማዳዊ አሠራር ፈጽሞ የተከለከለ ነው
ቃለ ዐዋዲውን ወይም ይህን ደንብ የሚቃረን ደንብ፤ መመሪያ እና ልማዳዊ አሠራር ፈጽሞ
የተከለከለ ነው::
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፲፭/15
ማንኛውም ምእመን ሕግጋተ ቤተ ክርስቲያንን
የሚተላለፍ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ነቅፎ
የሚያስነቅፍ፣ ክብረ ቤተ ክርስቲያንን ደፍሮ
የሚያስደፍር መሆን የለበትም።
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፲፬/14
የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አመሠራረትና አወቃቀር
በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ያልታወቀና ያል
ታቀፈ፤ በሀገረ ስብከቱ ወይም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም በቅዱስ
ሲኖዶስ ያልተፈቀደ ምንም ዓይነት የካህናት፣ የምእመናንና የሰንበት
ትምህርት ቤት ወጣቶች ማኅበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ስም መቋቋም አይችልም፡፡
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፯/7/መ
ከሰንበት ት/ቤት የሚመረጡት..
ከሰንበት ት/ቤት የሚመረጡት ዕድሜያቸው ከ 18 እስከ 35 ዓመት የሆናቸው፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማ፣ ቀኖናና ሥርዓት የማይጠረጠሩ
ወጣቶች የጾታ ልዩነት ሳይደረግ ይመረጣሉ፡፡ በሰበካው ሰንበት ት/ቤት በአባልነት የተመዘገቡ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የጸኑ፤...
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፲/10
ቃለ ዐዋዲ - አንቀጽ 64
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ፣ የአገልጋዮቿን ካህናት ኑሮ ለማሻ ሻልና ለልጆቿ ምእመናን የሚሰጠውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገል ግሎት ለማሟላት የወጣውን ይህን የቃለ ዐዋዲ ደንብና ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሥራ ላይ እንዳይውል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚቃወሙ ካህናት ከክህነታቸው፤ ምእመናን ከአባልነታቸው ይሠረዛሉ፡፡
ምእመን የሆነ ሁሉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ምእመን የሆነ ሁሉ
በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና
በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት መመራትና
በተወሰነለት የምእመንነት ደረጃ ጸንቶ በመኖር፣
መብቱ በሚፈቅድለት ሁሉ ቤተ ክርስቲያኑን
ማገልገል፣ ክርስቲያናዊ ግዴታና ኃላፊነት አለበት።
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፲፬/14
በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ
Popularበኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም በየደረጃው
የተቋቋሙና ወደፊትም የሚቋቋሙ የሰበካ መንፈሳዊ
ጉባኤያት ሁሉ ማእከሉ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ፤ ደንብ፤ መመሪያ፤
ትእዛዛትና ውሳኔዎች ይመራሉ።
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፲፭/15.1
ከቤተ ክርስቲያኒቱ ህብረት ይለያል ?
በንኡስ አንቀጽ ፩ መሠረት ይህ ደንብ እና ሕገ
ቤተ ክርስቲያኑ በሚፈቅደው አግባብ አደረጃጀቱን
እና ምዝገባ ሂደቱን ለማስተካከል ፈቃደኛ ያልሆነ
አጥቢያ እና አደረጃጀት እንደሁኔታው በቅዱስ
ሲኖዶስ ተገቢው ውሳኔ እና እርምት ይወሰድበታል
እንደአስፈላጊነቱም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ህብረት
ይለያል፡፡
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፲፱/19
ይህ ደንብ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከጸደቀበት ከጥቅምት ፳፻፲፮ ዓ.ም ጀምሮ በውጭ ሀገረ በሚገኙ አህጉረ ስብከት እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ሁሉ የጸና ይሆናል፡፡
Ethiopian Orthodox
Tewahedo Church Bylaw
July 2017 (Hamle 2009 E.C.)
This Ecclesiastical Constitution (Qale Awadee) shall be effective as of July 2017 (Hamle 2009 E.C.), the date it was approved and enacted by the Assembly of the Holy Synod.
PDF Download ማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህን፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ባልሰጠውና በሀገረ ስብከቱ አስተዳደራዊ መዋቅር
ሥር በማይመራ ማንኛውም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መስጠት ፈጽሞ አይችልም።
ቃለ አዋዲ - አንቀጽ ፲፮/17