Menu
PDF Download

EOTC BREAKING NEWS Feb. 17/2026

የአሜሪካው ፍርድ ቤት Feb. 17/2026 ቀን የደ.ም.ቅ.ሚካኤል ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ ክሱ ውድቅ ይደረግልኝ ብሎ ያስገባውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ በ14 ቀን ውስጥ በቀጥታ ለተከሰሱበት ጉዳይ ላይ ያላቸውን የአቁዋም ምላሽ ሁሉም አንዲያስገቡ በማዘዝ የከሳሽን የክስ መደብ በመደገፍ ውሳኔ አሳልፎዋል።

EOTC BREAKING NEWS Feb. 13/2026

የአሜሪካው ፍርድ ቤት Feb. 13/2026 ቀን በዋለው ችሎት በዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት እና በደ.ም.ቅ.ሚካኤል ካቴድራል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ላይ ምርመራ እንዲደረግባቸው ወሰነ።

የደ.ም.ቅ.ሚካኤል ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ በእንግሊዝኛ የተተረጎመ የመተደዳሪያ ደንብ ለፍርድ ቤት በማስገባት "ቃለ አዋዲ" የሚልን ቃልን ከአንግሊዝኛው መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ ጨርሶ በማውጣት እና በሌላ ቃል በመለወጥ ፍርድ ቤቱን በማሳሳት የማይገባ ውሳኔ አንዲያሳልፍ በማድረግ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ከሃዋሪያዊና ሲኖዶሳዊ አስተዳደር ለመገንጠል የተሰራው ማጭበርበር ለፍርድ ቤቱ አንዲታወቅ ተደርጎዋል። በልዩ ሁኔታ ምርመራ ይደረግበታል።

አግዚአብሄር አንድነታችንን አና ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ሰነድ ይመልከቱ።

አንደ ሱቅ የሚከፈቱ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ዘመን የሚያበቃበት ግዜ እየደረሰ ይመስላል።

Responsive image

ካህኑን የአሜሪካው ፍርድ ቤት አገዳቸው፤

ሃገረ ስብከቱ በ30 ቀን ውስጥ መልስ ካልሰጠ ይፈረድበታል።

የቤተክርስቲያን አንድነትን ለመበታተን እየሰሩ ስለሆነ

ላልሰማ ያሰሙ!

የዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት ፤ የደ.ም.ቅ.ሚ.ካ የሚገኙ ጥቂት ካህናትና መነኮሳት እንዲሁም የማህበረ ቅዱሳን አባላት እና የሰንበት ት/ቤት አባላት በአንድ ላይ ተባብረው በዲሲና አካባቢወ ሀገረ ስብከት የሚገኙ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃዋሪያዊ እና ሲኖዶሳዊ አስተዳደር ለመገንጠል እና በመናፍቃናዊ/በፕሮቴስታንት መዋቅር እንዲተዳደሩ ለማድረግ በዋሽንግተን ዲሲ ፍርድ ቤት ለማስወሰን እየተከራረከሩ ይገኛሉ።

ነገር ግን፤ ከዋናው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቀን በፊት 01/13/2026እ.ኤ.አ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ፍርድ ቤት ሃገረስብከቱን ወክሎ የጠበቃነት ፍቃድ ሳይኖረው በማጭበርበር የቤተክርስቲያንን አንድነት ለመገነጣጠል ይከራከሩ የነበሩትን ካህን ህገወጥ ስራ እየሰሩ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በማረጋገጥ ስለደረሰበት በማጭበርበር ላይ የነበሩትን ካህን ከዚህ በሁዋላ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን የመገነጣጠል ስራቸውን አንዳይሰሩ እና በሃገረ ስብከቱ በኩል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለመገነጣጠል የገባውን ሰነድ ውድቅ በማድረግ ካህኑ ፍርድ ቤት ተገኝተው መከራከር እንዳይችሉ አግዶአቸዋል::

ፍርድ ቤቱም በ 30 ቀን ውስጥ ሃገረስብከቱ ለተከሰሰበት ክስ በጠበቃ የተደገፈ ሙሉ መልስ (እንዴት አድርጎ አጥቢያ በቤተክርስቲያናትን ከሃዋሪያዊና ሲኖዶሳዊ አስተዳደር ለመገንጠል እንዳሰበ) በጽሁፍ መልስ የማያስገባ ከሆነ ሀገረ ስብከቱ ላይ ፍርድ እንደሚፈረድበት ፍርድ ቤቱ ገልጾ ውሳኔ አሳልፎዋል።

ስለሆነም፡ ከፍርድ ቤቱ ቀነ ቀጠሮ በፊት ለመላ አገልጋዩችና ህዝበ ክርስቲያኑ ጉዳዩን ለማሳወቅ እና ሁሉም ቤተክርስቲያኑን ነቅቶ እንዲጠብቅ የፍርድ ቤቱን ጉዳይ ለማስገንዘብ ይህ ጉባኤ ተዘጋጅቶዋል።

LIVE

ላልሰማ ያሰሙ!

January 25/2026 Sunday 05:00PM ከሰአት

በዋሽንግተን ዲሲ አቆጣጠር ለሁሉም ክፍት የሆነ የፍርድ ቤቱን ሁኔታ ለማስገንዘብ የቀጥታ ስርጭት ተዘጋጅቶዋል።

Loading...

Loading...

00 ቀን/Days
00 ሰአት/Hours
00 ደቂቃ/Minutes
00 ሰከንዶች/Seconds
The event ended check back this page for other meeting

ጉባኤው ለዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት በሃላፊነት ላይ ላሉ አባቶች ካህናት እንዲሁም ለሁሉም አገልጋይ ካህናት በየማእረጋቸው፤ በአለም ዙሪያ ለሚገኙ ምእመናን ፤ ለሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፤ ለማህበረ ቅዱሳን አባላት ሁሉ ክፍት ነው።

የቤተክርስቲያን ድምጽ ለመሆን በእለቱ በኢንተርኔት ጉባኤውን በመሳተፍ የበኩልዎን ይወጡ

© QaleAwadi.com . All rights reserved.